ስለ ሜሩቃ ኪድስ
ሜሩቃ ኪድስ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ጥበብ ከነገው የፈጠራና የቴክኖሎጂ ዓለም ጋር የሚያገናኝ የልጆች አዝናኝና አስተማሪ የዲጂታል ሚዲያ ተቋም ነው። በአኒሜሽን፣ በተረት፣ በሙዚቃና በእጅ ስራ አማካኝነት፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ ልጆችና ቤተሰቦች የፈጠራና የግኝት ዓለም እናዘጋጃለን።
የኢትዮጵያን ቅርስና እሴቶች ከአዳዲስ ሀሳቦች ጋር በማገናኘት፣ ልጆች እየተዝናኑ እንዲማሩ፣ በማንነታቸው እንዲኮሩ፣ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ጋር እንዲገናኙና ለነገው ትልቅ ራዕይ እንዲሰንቁ እንተጋለን።
በኢትዮጵያ ደመናዎች ውስጥ ተሰውረው፣ በሚያምሩ ድልድዮች የተገናኙ ተንሳፋፊ ደሴቶችን ያስቡ። እያንዳንዱ ደሴት ወደ አዲስ ግኝት የሚወስድ በር ይከፍታል። ጉጉ ልጆችንና አስተዋይ አስተማሪዎችን በመከተል፣ የተረት ዓለምን ከእውነተኛው ሕይወት ጋር የሚያገናኙ ጀብዱዎችን ያግኙ።
ስምንቱ ፕሮግራሞቻችን ልጆችን ለማዳመጥ፣ ለመፍጠር፣ ለመዘመር፣ ለመንቀሳቀስና ለማሰስ ይጋብዛሉ፦ የሜሩቃ ዓለም፣ የሜሩቃ መጽሐፍ ቤት፣ የሜሩቃ የልጆች ጊዜ፣ የሜሩቃ እጅስራ፣ የሜሩቃ አሻንጉሊቶች መንደር፣ ጉዞ ሜሩቃ፣ የሜሩቃ መዝሙሮች እና ሜሩቃ ዱብ ዱብ።
ዝግጅቶቻችን በዋናነት በአማርኛ የሚዘጋጁ ሲሆን፣ ሁሉም ልጆች በራሳቸው ቋንቋ እየተዝናኑ እንዲማሩ በተመረጡ የዩቲዩብ ዝግጅቶቻችን ላይ በኦሮሚኛ፣ በትግርኛ እና በእንግሊዝኛ የድምፅ ቅጂዎችን አካትተናል። በዩቲዩብ ማጫወቻው የቋንቋ መምረጫ (ቅንብሮች ➔ የድምፅ ትራክ) ውስጥ በመግባት የሚፈልጉትን ቋንቋ መምረጥ ይችላሉ።
በዌብሳይታችን፦ በዩቲዩብ ቻናላችን የሚለቀቁትን ፕሮግራሞች በተደራጀና ለአጠቃቀም በሚያመች የፕሌይሊስት አቀራረብ ለመመልከት፣ እንዲሁም አዝናኝ ጨዋታዎችን፣ መጻሕፍት እና ኮሚክሶችን እና ሱቅ ለማግኘት ዌብሳይታችንን መጠቀም ይችላሉ።
በአፕሊኬሽናችን፦ ሁልጊዜ በዌብሳይት ማሰሻ ከመግባት ይልቅ፣ ይዘቶቻችንን ይበልጥ በቀለለና በፈጠነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችለውን አፕሊኬሽኖች ክፍል በቀጥታ ከዌብሳይታችን ላይ ማውረድ ይችላሉ።
በቴሌግራም ቻናላችን፦ ልጆች በፕሮግራሞቻችን ላይ ያዩትን ተግባራዊ የሚያደርጉባቸው ልዩ ልዩ የፈጠራ ተግባራት የሚሰጡበት፣ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጋራ የሰሯቸውን የእጅ ስራዎች እና ፈጠራዎች ፎቶና ቪዲዮ እየላኩ የሚያጋሩበት የቴሌግራም መድረክ አዘጋጅተናል።
ድልድይ ወደ ነገ
ለቤተሰቦች፣ ለመምህራን እና ለፈጠራ አጋሮቻችን፦ merukakids@gmail.com
Rooted in home. Open to wonder.
Meruka Kids is an Ethiopian edutainment production brand connecting our rich cultural heritage with tomorrow’s creativity and technology. Through animation, stories, music, crafts and playful discovery, we create a world for children and families in Ethiopia and across the global diaspora.
We bring Ethiopian cultural connection and new possibilities together through joyful entertainment. Stories, music, making and movement give children different ways to explore, with curiosity leading the way. Our mission is to help children feel proud of their identity, connect with their mother tongues and imagine a brighter future.
Imagine floating islands hidden in the Ethiopian clouds, connected by beautiful bridges. Each island opens a different door to discovery. Meet curious children and caring mentors, travel between extraordinary places, and follow adventures that connect a fantasy world with real life.
Our eight original programs invite children to listen, make, sing, move and explore: Meruka World, Meruka Book Nook, Meruka Kids Time, Meruka Handcraft, Meruka Puppet Village, Guzo Meruka, Meruka Songs and Meruka Dub Dub.
Amharic is our original production language. Professional dubbing in Afaan Oromoo, Tigrinya and English is planned for supported YouTube episodes. When those audio tracks become available, select Settings → Audio track in the YouTube player to choose your language.
We hope every child finds something to wonder about, something to share and something that makes them feel connected. For parents and families, we are building a home for organized video playlists and creative resources, alongside cultural stories and family-focused updates on our social pages. Our first adventures are coming soon.
Bridge to Tomorrow
For families, educators and creative partners: merukakids@gmail.com